የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

የክልሉን መንግስት መ/ቤቶችንና ድርጅቶችን ሂሣብ ኦዲት ያደርጋል፣ ያስደርጋል፤

የክልሉ መንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች ያስገኙት ውጤት ህጉን የተከተለ፤ ኢኮኖሚያዊ በሆነ አሠራር የተፈጸመ መሆኑንና ተፈላጊውን ግብ መምታቱን ለማረጋገጥ የክዋኔና የአከባቢ ጥበቃ ኦዲት ያደርጋል፤ ያስደርጋል፡፡

የክልሉ መንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች አጠቃላይ የቁጥጥር ስርዓት በበቂ ሁኔታ መነደፉንና በትክክለኛ መንገድና በብቃት ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የሀብት ቁጥጥር ኦዲት ያደርጋል፤ ያስደርጋል፡፡

በመደበኛ ኦዲት ወቅት የአሰራር ግድፈት ወይም ጉድለት ከመገኘቱ የተነሣ አንድ ሂሣብ በልዩ ሁኔታ ኦዲት እንዲደረግ በምክር ቤቱ፤ በክልል ፍ/ቤቶች እና በሌሎች የመንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች አማካኝነት የተጠየቀ እንደሆነ በጉዳዩ ክብደት ላይ ተመስርቶ የእቅዱ አካል በማድረግ ልዩ ኦዲት ያደርጋል፡፡

የኦዲት ውጤቱ ከፍተኛ ጉድለት መከሰቱንና ወንጀል መፈፀሙን የሚያሣይ ሆኖ ሲገኝ ይህንኑ ለክልሉ ፍትህ ቢሮ፣ለክልሉ መስተዳድር ም/ቤትና ለሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ይልካል፡

ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መ/ቤቶችና ድርጅቶች እንዲሁም ከፌደራልና ከክልል ኦዲት መ/ቤቶች ጋር በመመካከር የኦዲት ደረጃ /ስታንዳርድ/ የአሰራር መወሠኛ መመሪያዎች ያወጣል፣

የክልሉ መንግሥት መ/ቤቶችና ድርጅቶች የገንዘብና ንብረት ሂሣብ አያያዝና አጠባበቅ አስመልክቶ በሚያዘጋጀው ማንኛውም ህጎች፡ደንቦችና መመሪያዎች ረቂቅ ሥራ ላይ አስፈላጊውን ምክርና አስተያየት ይሰጣል፣

የግል ኦዲተሮችንና የሂሣብ አያያዝ ባለሙያዎችን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለመስጠት ፣ ለማገድና ለመሠረዝ የሚያስችልና ወጥነት ያለው መመሪያ ያወጣል፡፡

የምስክር ወረቀቶችን በሚሰጥበትና በሚያድስበት ጊዜ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ የሚወሰነውን የአገልግሎት ዋጋ ያስክፍላል፡፡

ኃላፊነቱን በተሟላ ሁኔታ ለመወጣት ይቻለው ዘንድ መጽሐፎችን፡ መዘክሮችን፡ መዝገቦችን፡ ሠነዶችንና ሌሎች መረጃዎችን ለመመልከትና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት መረጃዎችን ዘገባዎችንና ትንተናዎችን ጠይቆ መቀበል ይችላል፡፡

የመ/ቤቱ ኦዲተሮች ሊከተሉት የሚገባውን ዝርዝር የሙያ ሥነ- ምግባር መመሪያ ያዘጋጃል፡፡

ከዚህ በላይ በሠፈሩ ድንጋጌዎች መሰረት ያከናወነውን የኦዲት ሥራ ውጤት ሪፖርት አግባብ ላለው የመንግስት መ/ቤት ወይም ለድርጅት የበላይ ኃላፊ ያሳውቃል፡፡

ከሚመለከታቸው መ/ቤቶችና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለውስጥ ኦዲተሮች ተገቢውን ስልጠናና የሙያ ምክር ይሰጣል፣ እንደአስፈላጊነቱም የውስጥ ኦዲት ሪፖርት እንዲቀርብለት ሊያደርግ ይችላል፡፡

አንድ ሂሣብ ወንጀል ባለበት ሁኔታና ታማኝነት በጐደለው አኳኋን መያዙን ለማመን ምክንያት ያለው እንደሆነ ይህንን ሂሣብ የሚመለከቱ ጹሁፎችን፣ መዘክሮችን፣ መዝገቦችን፣ ሰነዶችንና ከነዚህ ጋር ግንኙነት ባላቸው ሌሎች መረጃዎች ላይ በማሸግና በመመርመር ውጤቱን ለሚመለከተው ያሳውቃል፡፡

በክልሉ ውስጥ በኦዲት ሙያ ለሚሰማሩ ኦዲተሮችና የሂሣብ አያያዝ ሥራ ለሚያከናውኑ ለኦዲትና የሂሣብ አዋቂዎች በስራው መስክ ለማሠማራት የሚያስችላቸውን የሙያ ብቃት የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ያድሣል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል የሙያ ደረጃውን ጠብቀው ማከናወናቸውን ይከታተላል፡ ስልጠናና ምክር ይሰጣል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በህግ አግባብ ክስ ይመሰርታል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ እናትነሽ ማሩ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ እናትነሽ ማሩ ለመላዉ #የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓ.ም ለከተራ እና የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልካም…

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2018 ዓ.ም #የመጀመሪያ #ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃጸም ገመገመ።

(አሶሳ ፣ ጥር 6/2018 ዓ.ም )፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2018 በጀት የ6 ወራት የተከናወኑ ሥራዎችን ከመ/ቤቱ አመራሮች ፣ የመ/ቤቱ ማናጅመንት አባላት…

ኢትዮጵያ የህዝብ ፋይናንስ አስተዳደርን ለማሻሻል በተዘጋጀው የሳድኮፓክ ጉባኤ እየተሳተፈች ነው!

ኢትዮጵያ የህዝብ ፋይናንስ አስተዳደርን ለማሻሻል በተዘጋጀው የሳድኮፓክ ጉባኤ እየተሳተፈች ነው ፌዋኦ፣ ጥቅምት 18/2018፡- የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ የህዝብ ፋይናንስ ኮሚቴዎች ድርጅት (SADCOPAC) 17ኛው አመታዊ ኮንፈረንስ…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት በበጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች ተጠናክሮ መቀጠል አለባቸዉ ፦ ክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ እናትነሽ ማሩ!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት በበጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች ተጠናክሮ መቀጠል አለባቸዉ ፦ ክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ እናትነሽ ማሩ…